Poem

ውዴ…
አንቺ ማለት ለኔ እንደሻማ ቀልጠሽ
ጉልበትሽ ተሟጦ ብረሃን የሰጠሽ
የፍቅር መምህር አቦጊዳዬ ነሽ።
.
አንቺ ማለት ለኔ…
እንደ ውብ ጨረቃ ወጋገን ፈንጣቂ
ምድር ላይ ካሉቱ ለኔ የምትልቂ
ፍቅሬ ብቻ ሳትሆኜ እምነቴም ጭምር ነሽ
ለኔ የምትኖሪ ያንቺን ሁሉ ትተሽ።
.
ፍቅሬ…
ሀሰት በሞላባት በዚች ሞላጫ አለም
ለኔ ካንቺ ሌላ ጥሩ አፍቃሪ የለም
.
ስለዚህ…
መፃፍ ሳያቅተኝ ስለፍቅርሽ ቅኔ
‪#‎ህይወቴ‬ ነሽ አልኩሽ አንቺ ማለት ለኔ።

Comments