Skip to main content

Posts

Featured

Poem

‪#‎ አንቺ_ማለት_ለኔ‬ . ውዴ… አንቺ ማለት ለኔ እንደሻማ ቀልጠሽ ጉልበትሽ ተሟጦ ብረሃን የሰጠሽ የፍቅር መምህር አቦጊዳዬ ነሽ። . አንቺ ማለት ለኔ… እንደ ውብ ጨረቃ ወጋገን ፈንጣቂ ምድር ላይ ካሉቱ ለኔ የምትልቂ ፍቅሬ ብቻ ሳትሆኜ እምነቴም ጭምር ነሽ ለኔ የምትኖሪ ያንቺን ሁሉ ትተሽ። . ፍቅሬ… ሀሰት በሞላባት በዚች ሞላጫ አለም ለኔ ካንቺ ሌላ ጥሩ አፍቃሪ የለም . ስለዚህ… መፃፍ ሳያቅተኝ ስለፍቅርሽ ቅኔ ‪#‎ ህይወቴ‬  ነሽ አልኩሽ አንቺ ማለት ለኔ።

Latest Posts